ቱርክ ዜጎቿ ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች::

ባህርዳር፡ጥር 05 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዜጎች ወደ አሜሪካ ቢጓዙ ድንገተኛ እስር ሊጠብቃቸው ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ አሜሪካ መሄድ ያሰቡ የሃገሬው ዜጎች ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑት አሳስቧል።

የአሁኑ የአንካራ ማስጠንቀቂያ አሜሪካ በተመሳሳይ ሁኔታ ዜጎቿ ወደ ቱርክ እንዳይጓዙ ካስጠነቀቀች በኋላ የመጣ ነው ተብሏል።

አሜሪካ የቀድሞውን ቱርካዊ የባንክ ሰራተኛ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ከኢራን ጋር የተጣለውን ማዕቀብ በመተላለፉ በቁጥጥር ስር አውላዋለች።

ዋሽንግተን በኢራን ላይ የጣልኩት ማዕቀብ በተጣሰበትና በርካታ ቢሊየን ዶላሮች የገንዘብ ዝውውር በተደረገበት ህገ ወጥ ድርጊት ግለሰቡ እጁ አለበት ስትልም ከሳዋለች።

የግለሰቡ በቁጥጥር ስር መዋል ያልተዋጠላት አንካራም የአሜሪካን አካሄድ ተችታለች።
ድርጊቱም በፈረንጆቹ 2016 ተካሂዶ የከሸፈውን መፈንቅለ መንግስት መርተውታል ባለቻቸው ሃይማኖታዊ መሪ አማካኝነት የተቀነባበረ መሆኑንም ገልጻለች።

ቱርክ ዜጎቿ ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ አስጠንቅቃለች፡፡አሜሪካም በተመሳሳይ ዜጎቿ ወደ ቱርክ እንዳይጓዙ ከሰሞኑ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡
ሮይተርስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884704
  • Unique Visitors: 215541
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03