ተዘዋዋሪ ብድሩ ለታሰበለት ዓላማ እየዋለ አይደለም

 

ባህርዳር፡ጥር 25/2010 ዓ/ም(አብመድ)መንግሥት ለስራአጥ ወጣቶች ሥራ ማስጀመሪያ የለቀቀዉ ተዘዋዋሪ ብድር ሀብት ላፈሩና በማኅበር ተደራጅተው ለሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መሠጠቱ ቅሬታ እንዳሳደረባቸዉ የገንዳ ውኃ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

ተዘዋዋሪ ብድሩ ለወጣቶች የመጣ ቢሆንም ገንዘቡን እየተጠቀሙበት ያሉት ግን ሀብት ያፈሩና በማህበር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች እንደሆኑ የገንዳ ውሀ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በላይ ሞሴ ተናግሯል፡፡No automatic alt text available.

"ወጣቱ በተዘዋዋሪ ብድሩ እንዴት ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ጥልቅ ገንዛቤ ሳይሰጠው በመቅረቱ በዕድሉ ተጠቃሚ አልሆነም" የሚለው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ይህንን ክፍተት የተገነዘቡት በከተማዋ ውስጥ ሀብት ያፈሩና ከወጣትነት ዕድሜ የዘለሉ ግለሰቦች ከቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ጋር በመመሣጠር ገንዘቡን ያላግባብ እየተጠቀሙበት መሆኑን ተናግሯል ፡፡

የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ ሁሴን እንደተናገሩት በወጣቶቹ የተነሱት ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸው መሆኑን አምነው፣ በተለይ ከሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ የተሰጡትን ጥቆማዎች መሠረት ያደረገ ማጣራት ተካሂዶ በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ አብራርተዋል፡፡

‹‹በተዘዋዋሪ ብድሩ ጉዳይ የመጡ በርካታ ቅሬታዎች በእጃችን አሉ›› የሚሉት ከንቲባው ጉዳዩን ከቀበሌ ጀምሮ በማጣራት የተባለው ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ የእርምት እርምጃ ለመውሰድና በቀጣይ የብድር አገልግሎቱ በቀጥታ ለወጣቱ የሚደርስበትን አሠራር ለመፍጠር መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡

ደረጀ አምባው

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3300969
  • Unique Visitors: 189355
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03