ብአዴን ህብረ ብሄራዊነትን ባማከለ ሁኔታ ሀገራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

ባህር ዳር: ህዳር 11/2010(አብመድ) የብአዴን 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲከበር የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት ብአዴን በመማርና በመተራረም መርህ እየታደሰ ለሀገራዊ አንድነት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ 
የብአዴን መስመር በተከታታይ በሚካሄዱ ጥልቅ ተሀድሶዎች እየጠራ እና እየተስተካከለ፤ህዝባዊ ተጠቃሚነትን እያጎለበተ ይሄዳል ያሉት አቶ ደመቀ ብአዴን የመጣበት የተጋድሎ ታሪክ ዛሬ ለተገኘው ለውጥ ሁነኛ ማስተማሪያ ነው ብለዋል፡፡ 
በበዓሉ ላይ የአጋር ፓርቲ አባላት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡የኢህዴን/ብአዴን ታጋዮችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693155
  • Unique Visitors: 209288
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03