በጀርመን ዋንጫ ግምትን ያገኘው የባየርሙኒክና የዶርትመንድ ጨዋታ ባየርሙኒክን ወደ ሩብ ፍፃሜው አሳልፏል፡፡

ባህርዳር ፡ታህሳስ 12/2010 ዓ/ም(አብመድ)በሜዳው አልያንዝ አሬና የአምናውን የዚህን ዋንጫ ባለቤት ዶርትመንድን ያስተናገደው ባየር ሙኒክ 2ለ1 ነው ያሸነፈው፡፡

      ጆሮሜ ቦአቲንግና ቶማስ ሙለር የሙኒክን  ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ  አስገኝተዋል፡፡

      የዶርትሙንድን ብቸኛ ግብ በ77ተኛው ደቂቃ  ያርምሌንኮ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

       ኦባሚያንግን ሳያካትቱ ወደሜዳ የገቡት ቢጫ ለባሾች በአሌክሳንደር ኢሳክና ሶቅራጥሰ  የፈጠሯቸው የግብ ዕድሎች ለግብ የቀረቡ ነበሩ፡፡

     በሌሎች የጀርመን ዋንጫ ጨዋታዎች ባየር ሊቨርኩሰን  ቦርሲያ ሞንቸግላድባህን አሸንፏል፡፡

     ወርደር ብሬመን ፍራይበርግን 3ለ2 ኢንትራክት፣ ፍራንክፈርት ሄፌንሄምን 2ለ1 በመረታት ለሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284006
  • Unique Visitors: 188934
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03