በእንግሊዝ ለስራ ኃላፊዎች የሚከፈለው ደመወዝ የተጋነነ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል ፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 27/2009 ዓ/ም (አብመድ)በእንግሊዝ ከፍተኛ የስራ ኃላፈዎች የሚያገኙትን ደመወዝ ለመቀነስ ባለፉት አመታት ጥረት ቢደረግም እስካሁን ድረስ ከበታች ሰራተኛው ጋር ያለውን የክፍያ ልዩነት ማጥበብ አለመቻሉ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል ሲል ቢቢሲ ዘገበ ፡፡

 

በእንግሊዝ የከፍተኛ ክፍያ አጥኝ ማዕከል ቀደም ብሎ በ 1 መቶ ኩባንያዎች ውስጥ የሚገኙ ሃላፊዎች ብቻ የ 17 በመቶ የደመወዝ ቅነሳ መደረጉን ጠቅሶ በእንግሊዝ አንድ የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ በዓመት በአማካይ 28 ሺ ዩሮ ሲያገኝ የስራ ሃላፊዎች 160 ሺ ዩሮ እንደሚከፈላቸው አብራርቷል ፡፡ የከፍተኛ ክፍያ አጥኝ ማዕከል ዳይሬክተር ስቲፋን ስተርን እንደሚሉት የደመወዝ ልዩነቱ አሁንም እጅግ የተጋነነ ነው ፡፡

በተራው ሰራተኛ እና በሃላፊው መካከል ያለው የደመወዝ ልዩነት የማይጣጣም በመሆኑ በዚህ ዓመት የደመወዝ ልዩነቱን ለማስተካከል እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3300946
  • Unique Visitors: 189355
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03