በአዲሱ የባህርዳር ማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው እየተከበሩላቸው እንደሆነና የሙያ ስልጠናዎችንም እያገኙ መሆኑን ገለጹ

· ባህርዳር፡ጥር የካቲት 2 /2010 ዓ/ም(አብመድ)ማረሚያ ቤቱ በሰፊ ቦታ ላይ ያረፈና ከሚሠጣቸው የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎች በተጨማሪም መደበኛ ትምህርት ለመስጠት ምቹ መሆኑን ያነጋገርናቸው የህግ ታራሚዎች ገልፀውልናል፡፡

እንዲሁም ማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎቹ የሙያና ቴክኒክ ስልጠና በማዘጋጀት በስልጠና ያገኙትን ዕውቀት በተግባር ላይ እንዲያውሉ እድሉን ከማመቻቸቱ በተጨማሪ በመደበኛ ትምህርት ከአንደኛ እስከ አስረኛ ክፍል የሚማሩበት ምቹ ትምህርት ቤት ከፍቷል፡፡

ለአብነትም ከስልጠናው ባገኘው ዕውቀት እየሰራ ገቢ በማግኘት ከራሱ አልፎ ቤተሰቡን እያገዘ መሆኑን በሽመና ሙያ ላይ ያገኘነው ታራሚ አታላይ ደበበ ግልፆልናል፡፡

ስለሆነም ማረሚያቤቱ ለህግ ታራሚዎች ከቅጣትና የህግ አስተምህሮ ባለፈ ለዜጎች ትምህርትና ስልጠና የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነ የማረሚያ ቤቱ ማረምና ማነፅ ክፍል ኃላፊ አቶ ግርማ ቸኮል ገልፀዋል፡፡

የባህርዳር አዲሱ ማረሚያ ቤት ከጥቅምት አምስት 2010 ዓ.ም .ጀምሮ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በትዝታ ወይአንተ


Image may contain: one or more people, people standing, basketball court and outdoor


Image may contain: one or more people, people walking, people standing and outdoor

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870421
  • Unique Visitors: 214842
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03