በቻይና ሰው አልባ ተሸከርካሪ ጀልባ ስራ ላይ ዋለ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 4/2009 ዓ/ም (አብመድ)በሻንጋይ ይፋ የተደረገው ይህ ተሽከርካሪ ለእይታ የቀረበ ሲሆን ያለሰው በተንጣለለው ባህር ላይ ልምምዱን ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡

አብዛኛው ተመልካች ተሸከርካሪው የሚገጥሙትን መሰናክሎች በተገቢው ሁኔታ በማለፍ በትክክል ያለሰው ችግሮችን አልፎ የታዘዘው ቦታ ላይ በመድረስ ስራውን በጥራት አከናውኖ ተመልሷል፡፡

በወራት ልዩነት ወደ ገበያ ይቀርባል የተባለው ይህ የውሃ ላይ  ተሸከርካሪ ጀልባ በቅርብ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል የተሸከርካሪው ፈጣሪዎች ተናግረዋል፡፡

ተሸከርካሪው ለተለያዩ አገልግሎቶች ይውላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ባሕር ውስጥ የተለያዩ ካርታዎችን ለማንሳት የአካባቢውን የአየር ሁኔታ ለመከታተል ለጸረሽብር ተግባር አገልግሎት እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡       

ምንጭ፡-ሲጅቲኤን   

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537547
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03