በቅማንት የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ በተነሳባቸው 12 ቀበሌዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔ ሊያሰጥባቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 11/2009 ዓ/ም (አብመድ)በሰሜን ጎንደር ዞን ከአማራና በቅማንት የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ በተነሳባቸው 12 ቀበሌዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔ ሊያሰጥባቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚኖሩት የቅማንት ማህበረሰብ የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው የክልሉ ምክር ቤት በ2007 ዓ/ም 42 ቀበሌዎችን እንዲያስተዳድሩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ከ2007 ዓ/ም ወዲህ ደግሞ በየአካባቢያው በተደረጉ ውይይቶችና ህዝባዊ ስምምነቶች 21 ተጨማሪ ቀበሌዎች ወደራስ ገዝ አስተዳደሩ ሲካተቱ በ12 ቀበሌዎች ደግሞ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም የምክር ቤቱን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በ12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ ኢንዲደረግና ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ የጊዜ ሰሌዳውን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቧል፡፡

የቦርዱ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነጋ ዲፊሳ ‹‹ቀበሌዎቹ 12 ናቸው ፡፡34 ጣቢያዎች ይደራጃሉ፡፡ጎን ለጎንም የምርጫ አስፈጻሚዎችን እየመለመልን ነው፡፡ብቃቱ ያላቸውና ከህዝበ ውሳኔው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ይሳተፋሉ›› ብለዋል፡፡

አቶ ነጋ እንዳሉትም ከሚመለከታቸው የመስተዳደር አካላትም በዚህ ሂደት ውስጥ የጀመርንበት ሁኔታ አለ፡፡በቀጣይ ደግሞ የሚያስፈጽሙ ምርጫ አስፈጻሚዎች ፣የህዝብ ታዛቢዎች፣የሁለቱም ወገን ወኪሎች እና ከህዝቡ ጋር መድረክ ይዘናል ፡፡በየቀበሌው የህዝብ መድረክ ውይይቶች ይኖሩናል ፡፡በደምጽ አሰጣጡ ሂደት ህዝቡ ለመመዝገብ ሲመጣ ማሟላት ያለበትን ነገሮች ይዞ እንዶመጣ ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ እቅዶች ይዘናል ››ብለዋል፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አምሳሉ ደረጀ ሰላማዊ በሆነ ህዝቡ ምንም አይነት ስጋት ሳይኖርበት በነጻነት ወጥቶ የሚፈልገውን መወሰን እንዲችል የሚያደርጉ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የቅማንት ማንነት አስተዳደር ራስ ገዝ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን ሙላቱ በበኩላቸው የሚሰጠን ውሳኔ አግባበዊና ህጋዊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለማስፈጸም ዝግጁ ነን፡፡ለመቀበልም ዝግጁዎች ነን ብለዋል፡፡

ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀንም መስከረም 7/2010 ዓ/ም እንዲሆን ሀሳብ ቀርቧል፡፡

ደመወዝ የቆየ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3300940
  • Unique Visitors: 189354
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03