በቅማንት አስተዳደር እና በነባሩ አስተዳደር መካከል ያለውን ጥያቄ በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክርቤት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 1/2010 ዓ/ም (አብመድ)በቅማንት አስተዳደር እና በጎንደር አስተዳደር መካከል የነበረውን የአስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በፊት በተደረገው ህዝበ ውሳኔ መሰረት አጠቃላይ ምርጫ ከተደረገባቸው 8 ቀበሌዎች ውስጥ በህዝቡ ውሳኔ 7 የቀበሌ አስተዳደሮች ወደ ነባሩ አስተዳደር መጠቃለል እንደሚፈልጉ አረጋግጠዋል፡፡

አንድ ቀበሌ ደግሞ በቅማንት አስተዳደር ስር መሆን እንደሚፈልግ በህዝበ ውሳኔው አረጋግጧል ::

ይህን የህዝብ ውሳኔ የተመለከተው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረበለትን የህዝቡን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ሰባቱ ቀበሌዎች በነባሩ አስተዳደር አንዱ ቀበሌ ደግሞ በቅማንት አስተዳደር እንዲጠቃለሉ በሙሉ ድምጽ ዛሬ አጽድቋል፡፡

ሪፖርተር፡-ጋሻው ፈንታሁን/ከአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት/

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 2969184
  • Unique Visitors: 182518
  • Published Nodes: 2537
  • Since: 03/23/2016 - 08:03