በሰከላ ወረዳ በ 8.2 ሚሊየን ብር ዘመናዊ የአትሌቲክስ መንደር ለማቋቋም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ባህር ዳር፡ ሰኔ 19 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የአትሌቲክስ መንደሩ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ በሀገሪቱ አትሌቲክስ ዘርፍ እምርታ እንዲያመጣ ክትትል አደርጋለሁ ብሏል- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፡፡

በ 8.2 ሚሊየን ብር የሚገነባው የአትሌቲክስ መንደር በፍጥነት ለማጠናቀቅ ወረዳው ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፊዴሬሽን እና ከህዝብ ጎን ሆኖ እንደሚሰራ የሰከላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ አዱኛው ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፊዴሬሽን ፅ/ ቤት ሀላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ"ሰከላ ያለው የአየር ሁኔታ ና መልካዓምድራዊ አቀማመጥ ምቹ በመሆኑ የአትሌቲክስ መንደሩ ጥሩ የልምምድ ማዕከል ይሆናል ፡፡ድጋፋችንንም እናጠናክራለን ብለዋል፡፡


የኢትዮጲያ አትሌቲክስ ፊዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ እና ባለሀብት የሆኑት አቶ በላይነህ ክንዴ ለአትሌቲክስ መንደሩ እስከ አጋሮቻቸው ከ 1.4 ሚሊየን ብር በላይ ለግሰዋል፡፡ አቶ በላይነህ ክንዴ፣ በወረዳው ኢትዮጲያ ሆቴል የተሰኘ የአትሌቲክስ ክለብ አላቸው፡፡ክለቡ 30 አባላት ያሉት ሲሆን፣በተለያዮ አለምአቀፍ መድረኮች አሸናፊ የሆኑ አትሌቶችም አሉት፡፡ 
የሺሀሳብ አበራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284000
  • Unique Visitors: 188934
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03