ሻደይን በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል፡-የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 3/2009 ዓ/ም (አብመድ)የሻደይን በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሆነ የአማራ ክልል ባህል ና ቱሪዝም ቢሮ ገልጧል፡፡

ቢሮው በዓሉን በላሊበላ አሸንድየን፣በቆቦ ሶለል እና በሰቆጣ ሻደይን በሁሉም አካባቢዎች ያከብራል፡፡በቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንዲኖረውም ይደረጋል፡፡በሶስቱ አካባቢዎች 20 ልጃገረዶች ተመርጠው የባህል አምባሳደር ሆነው በየአካባቢዎች ያሳያሉ፡፡

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀይለየሱስ ፍላቴ እንደገለፁት ሻደይን በዋግ እና በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እንዲከበር ከሚዲያ ባለፈ፣ከቴሌ በመነጋገር በስልክ መልዕክት እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡ ሻደይን በዮኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በሰቆጣ ሻደይን በማስመልከት የንግድ ና ባዛር ዝግጅትም እየተሰናዳ ነው፡፡ስለሻደይ የተሰሩ ጥናቶች ይቀርባሉ፡፡ ሻደይ ብዙ ነገራቸው ተመሳሳይ ቢሆንም በላስታ አሸንድየ፣በራያ ሶለል፣በዋግ ደግሞ ሻደይ የሚል መጠሪያ አለው፡፡

ሻደይን ለማክበር 13 ቀናት ብቻ የቀሩ ሲሆን የሻደይ ልጃገረዶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው ለሻደይ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

ሻደይን በዋግ፣አሸንድየን በላስታ ላሊበላ፣ሶለልን በራያ በድምቀት እናክብር!!

የሺሀሳብ አበራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527366
  • Unique Visitors: 199329
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03