ሶማሊያ ሕገ-መንግስቷን ልትገመግም ነው፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 4/2009 ዓ/ም (አብመድ)የሶማሊያ መንግስት በሕገ-መንግስቱ ግምገማ ላይ ብሔራዊ ምክክር ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ ስትሆን አሁን ላይ ሂደቱን ለማሰጀመር ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመከናወን ላይ መሆኗን ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አብዱራህማን ሆሽ ጅብሪል እንደገለጹት ሂደቱ በአዲሱ ሕገ-መንግስት ውስጥ ሀሳባቸውን እንዲሰጡ እና የኔ የሚሉት ህገመንግስት እንዲኖራቸው ለማድረግ ሁሉም ሶማሊያውያን ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደሚሉት የሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በጣም ወሳኝ ናቸው ፡፡

ምክንያቱም የሕገ-መንግቱን መገምገም በጊዜ ገደቡ ማጠናቀቅ አለብን የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እስካስቀመጠው ጊዜ  መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

አብዱራህማን እንዳሉት "ይህ ሰነድ  ህጋዊነት እንዲኖረው እና በህዝቡ እስከመጨረሻው ተቀባይነት እንዲያገኝ  ወደ ህዝብ መውሰድ ያስፈልጋል የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሁሉ ሃሳብ እንዲሰጡበት ማድረግ ህገ-መንግስቱን ማንም ሰው እንደፈለገ እንዳይቀይረው ይልቁንም የሰው ብቻ መለዋወጥ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

በአገሪቱ በሚካሄደው ሁለንተናዊ ስብሰባ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዲካፈሉ የሚደረግ ሲሆን ቀጥሎም  በክልሎች እና በዲያስፖራዎች መካከል የውይይት መድረኮች ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም የጸደቀው ጊዜያዊ የሶማሊያ ህገ-መንግስት በህዝቡ ተሳትፎ እንደገና የሚሻሻል ይሆናል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537648
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03