ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣናቸው ወረዱ፡፡

ባህር ዳር: ህዳር 12/2010 (አብመድ)በቅርቡ ከዛኑፒኤፍ ፓርቲ ስልጣናቸው የወረዱት ሮበርት ሙጋቤ ዛሬ ደግሞ ከመከሰሳቸው በፊት ከፕሬዝዳንትነት እንዲለቁ ከተሰጣቸው ቀን በኋላ ከስልጣን ወርደዋል፡፡

ሮበርት ሙጋቤ ከ37 ዓመታት ፕሬዝዳንተነት መንበር በኋላ ከስልጣናቸው ወርደዋል፡፡
በራሴ ፈቃድ ከውሳኔ የደረስኩት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ስል ነው ብለዋል ውሳኔያቸውን ባሳወቁበት ደብዳቤ፡፡

ሮበርት ሙጋቤ ያባረሯቸው ምክትላቸው ኤመርሰን የፓርቲው ሊቀመንበር እንዲሆኑ መመረጣቸው ይታወቃል፡፡

ወታደራዊ ሀይሉ በወሰደው እርምጃ ዚምባብዌ እስካሁን በወታደራዊ ሀይሉ ስር ነች፡፡
የ93 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ የዚምባብዌ ብሄራዊ ጀግና እና የሀገሪቱ ታላቅ መስራች ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284055
  • Unique Visitors: 188936
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03