ሞሮኮ ወደ አውሮፓ የምትልከውን የኣትክልት እና ፍራፍሬ በ 2017 አጋማሽ ወደ 17 በመቶ ማሳደጓን አስታወቀች፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 4/2009 ዓ/ም (አብመድ)በሞሮኮ  ወደ አውሮፓ ህብረት የተላከው የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት በዚህ ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር, በ 17 ከመቶ ከፍ ብሏል፡፡

በ 2017 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች አጠቃላይ ዋጋ 551.8 ሚሊዮን ዩሮ (648 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) ሃገሪቱ ያስገባች ሲሆን ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሃገሪቱ 470.6 ሚሊዮን ዩሮ (553 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) ገቢ አግኝታ ነበር፡፡

በሃገሪቱ ውስጥ ገብቶ አትክልት እና ፍራፍሬ በማምረት እና ወደውጭ በመላክ የተሰማራው የስፔን አምራቾች ማህበር ለሃገሪቱ የአትክልት እና ፍራፍሬ እድገት ትልቁን ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡

ሞሮኮ ወደ አውሮፓ ህብረት ጥራታቸውን የጠበቁ እና ትኩስ ተወዳዳሪ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን በመላክ ቀዳሚውን ስፍራ በመያዝ የምትጠቀስ ሃገር ናት፡፡

ቲማቲም፣ ድንች እና ሽንኩርት ከሞሮኮ ወደ አውሮፓ የሚላኩ ምርቶች ናቸው፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሞሮኮ ወደ አውሮፓ ህብረት የምትልከውን የግብርና እና የምግብ ውጤቶችን ወደ 60 ከመቶ ከፍ ማድረግም ችላለች፡፡

ምንጭ፡-አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537654
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03