ማጉፉሊ ከታንዛንያ ተቃዋሚ መሪ ጋር ተወያዩ

ባህርዳር፡ጥር 03 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የታንዛኒያፕሬዝዳንትጆንማጉፉሊ ከዋናውየተቃዋሚመሪኤድዋርድሎዋሳእ.ኤ.አ. ከ2015 ምርጫወዲህ ለመጀመሪያጊዜዳሬሰላምውስጥ ተገናኝተው በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል ፡፡

ፕሬዝዳንትማጉፉሊ በፕሬዝዳንታዊምርጫጊዜከቀድሞውጠቅላይሚኒስትርጋርለመገናኘትፍላጎት እንዳላቸው እና በጋራ መስራት ይፈልጉ እንደነበር መረጃው አመልክቷል፡፡

‹‹ኤድዋርድሎዋሳከእኔጋርውይይት ለማድረግ በተለያዩጊዜያት ጠይቀዋል ››የሚሉት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ‹‹እናምይኸው ተገናኝተን ለሃገሪቱ በሚበጁ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ›› ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ‹‹በሁለታችን መካከል ያሉ መልካም ነገሮችን የተቀያየርን ሲሆን በጋራ ሃገራችንን ለማልማትም ተስማምተናል ››ማለታቸው ተዘግቧል ፡፡

የቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርድሎዋሳእ.ኤ.አ. በ2016 ወደገዢውየሲ.ሲ.ኤምፓርቲ ለመመለስፍላጎት ከማሳየት በላይም የሚል ቅሬታ የቀረበባቸው ሲሆን ሁኔታውንም  እንዲያመቻቹላቸው መጠየቃቸው እየተነገረ ነው፡፡

የተቀናቃኝፓርቲውመሪኤድዋርድሎዋሳመንግስት እያከናወነ ያለው ስራ ጥሩ ነው ሲሉ በቅርቡ ባስተላለፉት የምስጋና አስተያየት ላይ

"ፕሬዝዳንቱላከናወኑትመልካምሥራአመሰግናለሁ፡፡ለተከናወኑትስራዎችእውቅናመስጠትእናማበረታታትእንደሚያስፈልገንእንገነዘባለን ››ብለዋል ፡፡ 

በሁለቱ የፖለቲካ መሪዎች ስብሰባላይከተነሱ ጉዳዮች መካከል የኤሌክትሪክ ባቡር አገልግሎት እና 2ሺ አንድ መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግንባታ እንደሚገኝበት መረጃው አመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቶቹለብዙታንዛንያውያንየሥራዕድልእንደሚፈጥርላቸው የገለፁት ኤድዋርድሎዋሳለዚህ ዕድልም ፕሬዚዳንቱንከልብበማመስገን ውይይታቸው መልካም እንደነበር ተናግረዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527371
  • Unique Visitors: 199329
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03