ማንቸስተር ሲቲ ከ23 የፕሪሜርሊግ ጨዋታዎች በኋላ ሽንፈት ደረሰበት፡፡

ባህርዳር፡ጥር 07/2010 ዓ/ም(አብመድ)ትናንት ምሽት ከሊቨርፑል ጋር በአንፊልድ የተገናኘዉ ማንቸስተር ሲቲ በሊቨርፑል አስደንጋጭ ሽንፈት ደርሶበታል፡፡Image result for liverpool vs  man city

በመጀመሪያዉ አጋማሽ በቻምበርሊን ግብ መምራት የጀመረዉ ሊቨርፑል ባለቀ ደቂቃ በሳኔ አማካኝነት በገባበት ግብ 1 አቻ በመሆን ወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል፡፡

በሁለተኛዉ አጋማሽ  በፊርሚኒዮ ፣ሳላህ እና ማኔ ግሩም ግቦች  ሊቨርፑል እስከ 84ኛዉ ደቂቃ ድረስ 4ለ1 እየመራ ሙሉ ጨዋታዉን ተቆጣጥሮት ታይቷል፡፡Image result for liverpool vs  man city

ጨዋታዉ መገባደጃ ላይ ጉንዶጋንና ሲልቫ ባስቆጠሯቸዉ 2 ተከታታይ ግቦች ሊቨርፑል ዉጥረት ዉስጥ  ነበር፡፡ ጨዋታዉም 4ለ3 ሲሆን በሊቨርፑል በኩል ዉጥረት ነግሶ ነበር፡፡ማንቸስተር ሲቲም ያለመሸነፍ ጉዞዉን ለማስቀጠል ያደረገዉ ጉዞ አስፈሪ ነበር፡፡

ሆኖም ጨዋታዉ በሊቨርፑል 4ለ3 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል፡፡Image result for liverpool vs  man city

ማንቸስተር ሲቲ የአርስናልን ያአለመሸነፍ ክብረ ወሰን ላይ ሳይደርስ ቀርቷል፡፡

አርስናል 49 ጨዋታዎችን ሳይሸነፍ በ2003/4 የሊጉን ክብረወሰን መስበሩ ይታወሳል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870116
  • Unique Visitors: 214834
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03