ላይቤሪያውያን ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍን ለመተካት ነገ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 29/2010 ዓ/ም (አብመድ) የ 78 ዓመቷ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በሃገሪቱ ህገመንግስት መሰረት በስልጣን ላይ ሁለት የስድስት ዓመታት የስልጣን ጊዜያቸውን አጠናቀው በነገው ዕለት በሚደረገው ሃገራዊ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ለሚያገኘው ተወዳዳሪ ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡


በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተመርጠው ለሃገራቸው አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ ማን እንደሚተካቸው የሚታወቅ ይሆናል ፡፡


ሃያ ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከእነዚህ ተወዳዳሪዎች በተጨማሪ ለስድስት አመታት ግልጋሎት የሚሰጡ 73 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይመረጣሉ፡፡ 


አሁን ባለው መረጃ መሠረት 2.2 ሚሊየን ህዝብ በምርጫው ለመሳተፍ የተመዘገበ ሲሆን 20 ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ ፡፡ከዕጩዎቹ መካከል 2ቱ በግል 18ቱ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የወከሏቸው ናቸው፡፡


73 የህዝብ ተወካዮችን ለመምረጥ 986 እጩዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 824 (83.6 ) በመቶ ወንዶች ሲሆኑ፤ 162 ( 16.4 )በመቶ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ 
እንደ እ.ኤ.አ ጥቅምት 25 ደግሞ የመጨረሻው ውጤት እንደሚገለጽ የሃገሪቱ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527325
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03