Amhara News

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 09/2010 ዓ/ም(አብመድ)የኢፌዴሪ  ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ሰሞኑን ወደ ጎንደር እና ባህር ዳር ይመጣሉ፡፡ 
ምንጮቻችን እንደገለፁት በቆይታቸው ከህብረተሰቡ ጋር ይወያያሉ፡፡ 
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጉትን ውይይት ተከታትሎ የሚያቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ያስታውቃል፡፡

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 09/2010 ዓ/ም(አብመድ)ዛሬ ከሰዓት እንጨት የጫነ ኢነትሪ ቀበሌ 08 ከቦረና ሳይንት ከተማ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ ሀወይ ቦጣሶ በተባለ ቦታ ሲደርስ በመገልበጡ 4 ሰዎች ከባድ እና 3 ሰዎች ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው 2 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የስራ ሂደት መሪ ኢንስፔክተር ሰኢድ አብዱ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስታውቀዋል፡፡Image may contain: shoes and outdoor

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 09/08/2010 ዓ/ም (አብመድ)በቅርቡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው ጥልቅ ግምገማ ከመድረክ ውይይት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ተግባር እንግባ፣ ህዝቡ ሲጠይቀን የነበረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ወርደን በመፍታትና ምላሽ በመስጠት ህዝቡ በአመራሩ ላይ ያጣውን እምነት በላቀ ሁኔታ ተቀራርቦ ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ የተግባር አመራር እንስጥ በሚል ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ ይታወቃል፡፡

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 06/2010 ዓ/ም (አብመድ) የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ በኢህአዴግና ብአዴን ደረጃ የተከናወኑ ውይይቶች የደረሱበትን ክንዋኔ አስመልክቶ ከሚያዝያ 4 ጀምሮ ለ2 ቀናት ተወያይቷል፡፡ Image may contain: one or more people, people sitting, screen and indoor

ወልዲያ ከፋሲል ከነማ ዛሬ አማራ ደርቢ እግር ኳስ ጨዋታ ይደረጋል፡፡19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልዲያ ላይ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

ባህርዳር፡ጥር 30/2010 ዓ/ም(አብመድ)ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሜካኒካል እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ያገኙ 62 ተማሪዎችን ተቀብሎ በባህር ላይ ምህንድስና በማሠልጠን አስመርቋቸዋል፡፡

ባህርዳር፡ጥር 26/2010 ዓ/ም(አብመድ)በክልላችን ሁለተናዊ ልማት ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንዲሁም የህዝቡን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ሰፊ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዘርፈ ብዙ ተግባር በመንግስትና በመላው ህብረተሰብ የተቀናጀ ጥረት ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሀገራችንንም ሆነ የክልላችንን ተስፋ ያለመለሙ ለውጦችና ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ ይህም ውጤት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት የራሱን አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ መጥቷል፡፡ በቀጣይነትም ይህንኑ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግና ለማስፋት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ባህርዳር፡ጥር 24/2010 ዓ/ም(አብመድ)አቶ ዘውዱ በዛ ይባላሉ፡፡የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡በግንባታ ስራ በሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ፡፡Image may contain: 1 person, closeup

ባህርዳር፡ጥር 25/2010 ዓ/ም(አብመድ)ወጣት አንለይ በለጠ ይባላል፡፡በባህዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ አውስኮድ አደባባይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለባለፉት አምስት ዓመታት ጫማ በማሳመር ይተዳደር ነበር፡፡ወጣቱ ከጠዋት 1 ሰዓት ተኩል ጀምሮ እስከ ምሽት 1 ሰዓት ድረስ ስራ ቦታው ላይ ይገኛል፡፡
በማንኛውም ሰዓት የሄደ ሰው አያጣውም፡፡ እርሱም በርካታ ደንበኞች አሉት እና ስራውን ደስ እያለው ይስራል፡፡አሁን አሁን ግን ለአንለይ ስራ አስቸጋሪ የሆነ ጤና መታወክ ችግር አጋጥሞታል ፡፡ አፍንጫውን ስለሚያፍነው መተንፈስ ያሰቸግረዋል፡፡

Visitors

  • Total Visitors: 3161951
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03